1 ሳሙኤል 13:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን በማክማስ ሰፍረው በነበረበት ጊዜ ሳኦል፣ ልጁ ዮናታንና ዐብረዋቸው የነበሩት ሰዎች በብንያም ግዛት በምትገኘው በጌባዕ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ ነበሩ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች ግን በሚክማስ ሰፍረው ነበር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ መሸጉ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችም ምሽግ በሚክማስ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልና ልጁ ዮናታንም፥ ከእነርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ በብንያም ገባዖን ተቀምጠው አለቀሱ፤ ፍልስጥኤማውያንም በማኪማስ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ በብንያም ጊብዓ ተቀመጡ፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ ሰፈሩ። |
ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ዮናታን ጌባዕ የነበረውን የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር መታ፤ ፍልስጥኤማውያንም ይህን ሰሙ። ሳኦልም፣ “ዕብራውያን ይስሙ!” በማለት በምድሪቱ ሁሉ መለከት አስነፋ።