1 ሳሙኤል 13:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልክ መሥዋዕቱን አቅርቦ እንዳበቃ፣ ወዲያውኑ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም እንዲመርቀው ሊቀበለው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልክ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርቦ እንዳበቃ፥ ወዲያውኑ ሳሙኤል ደረሰ፤ እርሱም ሊቀበለው ወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም መሥዋዕት የማቅረቡን ሥርዓት እንደ ፈጸመ ወዲያውኑ ሳሙኤል ደረሰ፤ ሳኦልም ወጥቶ አቀባበል አደረገለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማሳረግ በፈጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙኤል መጣ፤ ሳኦልም እንዲባርከው ሊገናኘው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ። የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ማሳረግ በፈጸመ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሳሙኤል መጣ፥ ሳኦልም እንዲመርቀው ሊገናኘው ወጣ። |
በዚሁ ጊዜ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ ዐጫጆቹንም፣ “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሁን!” ብሎ ሰላምታ ሰጣቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ይባርክህ!” ብለው መለሱለት።
ከአገልጋዮቹ አንዱ ለናባል ሚስት ለአቢግያ እንዲህ አላት፤ “እነሆ፤ ዳዊት ሰላምታውን እንዲያቀርቡለት ከምድረ በዳ ወደ ጌታችን መልእክተኞችን ልኮ ነበር፤ እርሱ ግን የስድብ ናዳ አወረደባቸው።