እንዲሁም አበኔር ለብንያማውያን ራሱ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ።
1 ሳሙኤል 10:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የብንያምን ነገድ በየጐሣው ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ጐሣም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የብንያምን ነገድ በየወገኑ ወደ ፊት አቀረበ፤ የማጥሪ ቤተሰብም ተመረጠ። በመጨረሻም የቂስ ልጅ ሳኦል ተመረጠ። እርሱ ግን ተፈልጎ አልተገኘም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገናም ሳሙኤል፥ የብንያም ነገድ ቤተሰቦች ሁሉ ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከነዚያም የማጥሪ ቤተሰብ በዕጣ ተመረጠ፤ በመጨረሻም የማጥሪ ቤተሰብ ወንዶች ወደፊት እንዲቀርቡ አደረገ፤ ከእነርሱም መካከል ለቂስ ልጅ ለሳኦል ዕጣ ወጣ፤ እነርሱም በፈለጉት ጊዜ ሊያገኙት አልቻሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፤ ዕጣውም በማጥር ወገን ላይ ወደቀ፤ የማጥርንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፤ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፤ ፈለገውም፤ አላገኘውምም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የብንያምንም ነገድ በየወገናቸው አቀረበ፥ ዕጣውም በማጥሪ ወገን ላይ ወደቀ። የማጥሪንም ወገን በየሰዉ አቀረበ፥ ዕጣውም በቂስ ልጅ በሳኦል ላይ ወደቀ፥ ፈለጉትም፥ አላገኙትምም። |
እንዲሁም አበኔር ለብንያማውያን ራሱ ሄዶ ይህንኑ ነገራቸው፤ ከዚያም እስራኤልና መላው የብንያም ቤት ለማድረግ የፈለጉትን ሁሉ ለዳዊት ለመንገር ወደ ኬብሮን ሄደ።
ከዚያም መርከበኞቹ እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ክፉ ነገር በማን ምክንያት እንደ መጣብን ለማወቅ፣ ኑ ዕጣ እንጣጣል” ተባባሉ። ዕጣም ተጣጣሉ፤ ዕጣውም በዮናስ ላይ ወደቀ።
ከዚያም ሕዝቡ ንጉሥ እንዲያነግሥላቸው ለመኑት፤ እግዚአብሔርም ከብንያም ወገን፣ የቂስን ልጅ ሳኦልን ሰጣቸው፤ እርሱም አርባ ዓመት ገዛቸው።
ቂስም ከእስራኤል ልጆች መካከል በመልከ ቀናነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፣ ቁመቱም ከሌሎቹ ሁሉ ይልቅ ከትከሻው በላይ ዘለግ ያለ፣ ሳኦል የተባለ ወጣት ልጅ ነበረው።