1 ቆሮንቶስ 9:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚመረምሩኝ የምሰጠው መልስ ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሐዋርያነት መብት የለህም” ብለው የሚተቹኝ ቢኖሩ የምሰጠው መልስ ይህ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚከራከሩኝ መልሴ እንዲህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሚመረምሩኝ መልሴ ይህ ነው። ልንበላና ልንጠጣ መብት የለንምን? |
“እኔም፣ ተከሳሽ በከሳሾቹ ፊት ቆሞ ለተከሰሰበት ነገር መልስ ለመስጠት ዕድል ሳያገኝ፣ አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ እንዳልሆነ ነገርኋቸው።
ከእናንተ ርቄ ሳለሁ እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ሥልጣኔን በኀይል እንዳልጠቀም ነው፤ ጌታም ይህን ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ ለማፍረስ አይደለም።
በእምነት መሆናችሁን ለማወቅ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ። ከፈር የወጣችሁ ካልሆነ በቀር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ እንዳለ አታውቁምን?
በልቤ ስላላችሁ እና በእስራቴም ሆነ ለወንጌል ስመክትና ሳጸናው ሁላችሁም ከእኔ ጋራ የእግዚአብሔር ጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፣ ስለ ሁላችሁ እንዲህ ማሰቤ ተገቢ ነው።