ዘካርያስ 6:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይለኞቹ ፈረሶች በወጡ ጊዜ ምድርን ለመቃኘት ተጣድፈው ነበር፤ መልአኩም “ሂዱ፤ ምድርን ቃኙ!” አላቸው፤ እነርሱም ምድርን ቃኙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠንካሮቹ ፈረሶች ሲወጡ፣ በምድር ሁሉ ለመመላለስ አቈብቍበው ነበር። እርሱም፣ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጠንካሮቹ ፈረሶች ሲወጡ፥ በምድር ሁሉ ለመመላለስ አቈብቁበው ነበር፤ እርሱም፥ “ወደ ምድር ሁሉ ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወደ ምድር ሁሉ ሄዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጋላዎቹም ደግሞ ወጡ በምድርም ይመላለሱ ዘንድ ለመሄድ ይፈልጉ ነበር፣ እርሱም፦ ሂዱ፥ በምድር ላይ ተመላለሱ አለ። እነርሱም በምድር ላይ ተመላለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጋላዎቹም ደግሞ ወጡ በምድርም ይመላለሱ ዘንድ ለመሄድ ይፈልጉ ነበር፥ እርሱም፦ ሂዱ፥ በምድር ላይ ተመላለሱ አለ። እነርሱም በምድር ላይ ተመላለሱ። |
እግዚአብሔር መላውን ዓለም አተኲሮ በመመልከት፥ በሙሉ ልባቸው በእርሱ ለሚተማመኑት ሁሉ ብርታትን ይሰጣቸዋል፤ እንግዲህ አንተ የሞኝነት ሥራ ስለ ፈጸምክ ከእንግዲህ ወዲህ ጦርነት አይለይህም፤”
“ከዚህ በኋላ ከሌሎቹ አውሬዎች ሁሉ ልዩ ስለ ነበረው ስለ አራተኛው አውሬ በይበልጥ ለማወቅ ፈለግኹ፤ ይህ አውሬ እጅግ አስፈሪ የሆነ፥ ዐድኖ ያገኘውን ሁሉ በብረት ጥርሶቹና በነሐስ ጥፍሮቹ ሰባብሮና ቦጫጭቆ የሚበላ፥ የተረፈውንም በእግሩ የሚረጋግጥ ነበር።
ዐሥሩ ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡት ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ከዚያን በኋላ ከበፊተኞቹ ነገሥታት የተለየ ሌላ ንጉሥ ተነሥቶ ከዐሥሩ መንግሥታት ሦስቱን ይገለብጣል፤
እስራኤላውያን በኤዶም ግዛት ዙሪያ ለመሄድ አስበው ከሖር ተራራ ተነሥተው ወደ ቀይ ባሕር በሚወስደው መንገድ ተጓዙ፤ ነገር ግን በመንገድ ሳሉ የሕዝቡ ትዕግሥት አለቀ፤