ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሺህ የሚቈጠር ብዛት ይኖራቸዋል፤ ከእነርሱም ደካሞች የነበሩት ኀያል ሕዝብ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ በጊዜው ፈጥኖ እንዲፈጸም አደርጋለሁ።”
ዘካርያስ 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ ምድር እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦር እሰበስባቸዋለሁ፤ ቦታ እስኪጠባቸው ድረስ በገለዓድና በሊባኖስም ጭምር አሰፍራቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከግብጽ እመልሳቸዋለሁ፤ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ አመጣቸዋለሁ፤ በቂ ስፍራም አይገኝላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ። የሚበቃ ስፍራ እስኪጠባቸው ድረስ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፣ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከግብጽም ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ ከአሦርም እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገለዓድና ወደ ሊባኖስ ምድር አመጣቸዋለሁ፥ የሚበቃም ቦታ አይገኝላቸውም። |
ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሺህ የሚቈጠር ብዛት ይኖራቸዋል፤ ከእነርሱም ደካሞች የነበሩት ኀያል ሕዝብ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ በጊዜው ፈጥኖ እንዲፈጸም አደርጋለሁ።”
“የይሁዳ ነገሥታት ቤተ መንግሥት የገለዓድን አገርና የሊባኖስን ተራራዎች ያኽል ለእኔ የተዋበ ነው፤ ነገር ግን ማንም የማይኖርበት ባድማ አደርገዋለሁ።
የእስራኤልንም ሕዝብ ወደ ምድራቸው እመልሳለሁ፤ በቀርሜሎስ ተራራና በባሳን አውራጃ የሚበቅለውን ሁሉ ይመገባሉ፤ በኤፍሬምና በገለዓድ ከሚበቅለውም እህል የፈለጉትን ያኽል ይመገባሉ፤
እንደ ወፍ ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር እየበረሩ ይመጣሉ፤ ወደ መኖሪያቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ይህን የምናገር እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።”
በስደት ላይ የነበሩት የሰሜን እስራኤል ሕዝብ ሖላ ከሚባል አገር ተመልሰው የከነዓንን ምድር እስከ ሰራጵታ ድረስ ይወርሳሉ፤ በሰፋራድም የሚኖሩ የኢየሩሳሌም ስደተኞች በስተ ደቡብ ያሉትን ከተሞች ይይዛሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! የአንተ መንጋ የሆነውን ሕዝብህን በሥልጣንህ ጠብቅ፤ እነርሱም በለመለመ አትክልት ቦታ መካከል በጫካ ውስጥ ብቻቸውን የሚኖሩ ናቸው፤ እንደ ቀድሞው ዘመን በባሳንና በገለዓድ እንዲመገቡ አድርጋቸው።