ሮሜ 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በፈጸመው በአዳኝነት ሥራ በእግዚአብሔር ጸጋ ብቻ ይጸድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲሁ በጸጋው ይጸድቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽድቅ ግን በኢየሱስ ክርስቶስም ቤዛነት ያለ ዋጋ በእርሱ ቸርነት ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ። |
ስለዚህ ተስፋው የተመሠረተው በእምነት ላይ ነበር፤ ይህም ተስፋ ለአብርሃም ዘሮች ሁሉ ከእግዚአብሔር በጸጋ የተሰጠ መሆኑ በዚህ ተረጋግጦአል። ይህም ሕግን ለሚከተሉት ሰዎች ብቻ ሳይሆን እንደ አብርሃም ላመኑ ሁሉ ነው፤ በዚህም መሠረት አብርሃም የሁላችንም አባት ነውና።
እናንተን ግን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ አደረገ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስን ጥበባችን፥ ጽድቃችን፥ ቅድስናችንና ቤዛችን እንዲሆን አደረገው።
ከእናንተም አንዳንዶቻችሁ እንዲሁ ነበራችሁ፤ አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ከኃጢአት ታጥባችኋል፤ ለእግዚአብሔር የተለየ ቅዱስ ሕዝብ ሆናችኋል፤ ጸድቃችኋልም።
ሰዎችን ሁሉ ከኃጢአት ለመዋጀት ራሱን ቤዛ አድርጎ የሰጠ እርሱ ነው፤ ይህም ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ የእግዚአብሔርን የማዳን ሥራ የሚያስረዳ ምስክርነት ነው።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤
እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤