እነሆ፥ ጥፋትን የስሜ መጠሪያ በሆነችው ከተማ እጀምራለሁ፤ ታዲያ ከቅጣት የሚያመልጡ ይመስላቸዋልን? እኔ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ጦርነትን ስለማመጣ ከቶ ከቅጣት የሚያመልጡ የሉም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።
ሮሜ 11:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት አይሁድ ካልራራላቸው ለእናንተም አይራራላችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራላቸው፣ ለአንተም አይራራልህምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር በተፈጥሮ ቅርንጫፎች ለሆኑት ካልራራላቸው ለአንተም አይራራልህምና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በተፈጥሮአቸው ቅርንጫፎች ለነበሩ ለእነዚያ ከአልራራላቸው ለአንተም አይራራልህም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንደ ተፈጠሩት ለነበሩት ቅርንጫፎች የራራላቸው ካልሆነ ለአንተ ደግሞ አይራራልህምና። |
እነሆ፥ ጥፋትን የስሜ መጠሪያ በሆነችው ከተማ እጀምራለሁ፤ ታዲያ ከቅጣት የሚያመልጡ ይመስላቸዋልን? እኔ በምድር በሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ላይ ጦርነትን ስለማመጣ ከቶ ከቅጣት የሚያመልጡ የሉም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።
“እንግዲህ መቀጣት የማይገባቸው ሰዎች እንኳ የቅጣቱን ጽዋ ገፈት የሚቀምሱ ከሆነ እናንተ ያለ ቅጣት የምታመልጡ ይመስላችኋልን? አይደለም፤ እናንተም ከቅጣቱ ጽዋ መጠጣት አለባችሁ።
እንደ ጓሮ የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆኑ አይሁድ ተቈርጠው ቢወድቁና እናንተ እንደ ዱር የወይራ ዛፍ ቅርንጫፎች የሆናችሁ አሕዛብ በቦታቸው ተተክታችሁ የእነርሱን ሀብትና በረከት ተካፋዮች ብትሆኑ፥
አባባላችሁስ ልክ ነው፤ ነገር ግን እነርሱ ተቈርጠው የወደቁት ባለማመናቸው ሲሆን እናንተ ጸንታችሁ የቆማችሁት በማመናችሁ ነው፤ ታዲያ፥ መፍራት እንጂ መታበይ አይገባችሁም።
እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ።
ይህን ሁሉ አስቀድማችሁ አንድ ጊዜ የምታውቁት ቢሆንም እንኳ ጌታ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አውጥቶ እንዳዳነና ያላመኑትንም በኋላ እንዳጠፋቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።