ሮሜ 10:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢሳይያስም፦ “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ‘እግዚአብሔር የት ነው?’ ብለው ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ፤” በማለት ደፍሮ ተናግሮአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢሳይያስም በድፍረት፣ “ላልፈለጉኝ ተገኘሁላቸው፤ ላልጠየቁኝም ራሴን ገለጥሁላቸው” ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ኢሳይያስም በድፍረት “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ” አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢሳይያስም ደፍሮ፥ “ለአልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ለአልጠየቁኝም ተገለጥሁላቸው” ብሏል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብሎአል። ኢሳይያስም ደፍሮ፦ ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፥ ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ አለ። |
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የያዕቆብን ነገዶች ክብር እንደገና ለማንሣትና የተረፉትን እስራኤላውያን ለመመለስ አገልጋዬ ሆነህ መሥራት ብቻ አይበቃም። ከዚህ የበለጠ ግን አዳኝነቴ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርስ ዘንድ አንተ ለሕዝቦች ሁሉ ብርሃን እንድትሆን አደርግሃለሁ።” ይላል።
ቀድሞ ያልተነገራቸውን ነገር ስለሚያዩና ያልሰሙትን ነገር ስለሚያስተውሉ ብዙ ሕዝቦች ስለ አገልጋዬ ይደነቃሉ፤ ነገሥታትም በእርሱ በመደነቅ የሚናገሩትን ያጣሉ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ድምፅህን ሳትቈጥብ ጩኽ! ድምፅህ እንደ እምቢልታ ከፍ ይበል! ለሕዝቤ ለእስራኤል ዐመፃቸውንና ኃጢአታቸውን ንገራቸው።
ስለዚህ የቤቱ ጌታ አገልጋዩን እንዲህ አለው፦ ‘ቤቴ እንዲሞላ ወደ ገጠር በሚወስዱት ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂደህ ሌሎች እንዲመጡ አድርግ!