ራእይ 2:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት፤ እርስዋ ግን ከዝሙትዋ ንስሓ መግባትን አልፈለገችም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዝሙቷ ንስሓ እንድትገባ ጊዜ ሰጥቻት ነበር፤ እርሷ ግን ፈቃደኛ አልሆነችም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንስሓም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሓ መግባትን አልወደደችም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንስሓም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሓ እንድትገባ አልወደደችም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም። |
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።
አንዳንድ ሰዎች እንደሚመስላቸው ጌታ የተናገረውን የተስፋ ቃል ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃና ማንም ሰው እንዳይጠፋ ፈልጎ ስለ እናንተ ይታገሣል።
ሰዎች በታላቅ ግለት ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ንስሓ አልገቡም፤ እርሱንም አላከበሩም።