በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።
ራእይ 16:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ፣ አንተም ደግሞ ደም እንዲጠጡ አደረግሃቸው፤ ይህ የሚገባቸው ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቅዱሳንንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፤ የሚገባቸው ነውና፤” ብሎ ሲናገር ሰማሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቅዱሳንና የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ። |
በተለይም ምናሴ የንጹሓን ሰዎችን ደም በማፍሰሱና ኢየሩሳሌምንም በንጹሓን ደም በመሙላቱ ምክንያት ይህ ሁሉ ሊፈጸም ችሎአል፤ ከዚህም የተነሣ እግዚአብሔር ለምናሴ ምሕረት ሊያደርግለት አልፈቀደም።
አሁን ግን በሚያደርገው ነገር የእግዚአብሔርን ማንነት በግድ ታውቃለህ፤ እነሆ፥ እኔ በዚህ በትር የአባይን ወንዝ ውሃ እመታለሁ፤ ውሃውም ወደ ደም ይለወጣል።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
ካህናቱና ነቢያቱ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው የተናገረውን ሁሉ እናንተ ራሳችሁ ሰምታችሁታል፤ በከተማችን ላይ ክፉ የትንቢት ቃል በመናገሩ ሞት ይገባዋል።”
ከዚህ በኋላ መሪዎቹና ሕዝቡ፦ “ይህ ሰው የተናገረን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ስለ ሆነ ሞት አይገባውም” ሲሉ ለካህናቱና ለነቢያቱ ተናገሩ።
ነገር ግን የጌታውን ፈቃድ ባለማወቅ፥ ቅጣት የሚያመጣበትን ነገር አድርጎ ቢገኝ ቅጣቱ ይቀልለታል፤ ብዙ ከተሰጠው ሰው ብዙ ይፈለግበታል፤ ብዙ ዐደራም ከተሰጠው ሰው፥ ብዙ ይጠበቅበታል።”
ታዲያ፥ የእግዚአብሔርን ልጅ የናቀ፥ የተቀደሰበትን የቃል ኪዳን ደም ያረከሰ፥ የጸጋን መንፈስ የሰደበ፥ እንዴት ያለ የባሰ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል!
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”
“ለመማረክ የተመደበ ይማረካል፤ በሰይፍ ለመገደል የተመደበ በሰይፍ ይገደላል፤” እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚያስፈልገው በዚህ ጊዜ ነው።
ሁለተኛው አውሬ ለመጀመሪያው አውሬ ምስል የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን ተሰጠው፤ የሕይወት እስትንፋስ ለመስጠት ሥልጣን የተሰጠውም ምስሉ ለመናገር እንዲችልና ለእርሱ የማይሰግዱት ሁሉ እንዲገደሉ ያደርግ ዘንድ ነው።
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!
ፍርዱ እውነትና ትክክል ነው፤ ምድርን በአመንዝራነትዋ ያረከሰችውን ታላቂቱን አመንዝራ በፍርድ ቀጥቶአታል፤ እርስዋን በመቅጣትም የአገልጋዮቹን ደም ተበቅሎአል።”