ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ የሚፈጸምባቸውን የመጨረሻ የሆኑትን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙትን ሰባት መላእክት አየሁ።
ራእይ 11:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለተኛው ወዮ አለፈ፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ ቶሎ ይመጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለተኛው ወዮ ዐልፏል፤ እነሆ፤ ሦስተኛው ወዮ ቶሎ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለተኛው ወዮ አልፎአል፤ እነሆ፥ ሦስተኛው ወዮ በቶሎ ይመጣል። |
ሌላም ታላቅና ድንቅ ምልክት በሰማይ አየሁ፤ የእግዚአብሔር ቊጣ የሚፈጸምባቸውን የመጨረሻ የሆኑትን ሰባት መቅሠፍቶች የያዙትን ሰባት መላእክት አየሁ።
ከዚህ በኋላ ስመለከት አንድ ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት የእምቢልታቸውን ድምፅ በሚያሰሙበት ጊዜ በምድር ላይ ለሚኖሩ ሰዎች ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!” እያለ ሲጮኽ ሰማሁ።