አንተ እግዚአብሔርን መከታህ፥ ልዑል አምላክንም ጠባቂህ አድርገሃል።
“እግዚአብሔርን መሸሸጊያ፣” ልዑልንም መጠጊያህ አድርገኸዋልና።
ጌታን፥ “አንተ ተስፋዬ ነህ” ብለህ፥ ልዑልን መጠጊያህ አድርገሃልና።
አቤቱ፥ እነሆ፥ ጠላቶችህ ይጠፋሉና፥ ዐመፃንም የሚሠሩ ሁሉ ይበተናሉና።
በምሄድበት ቦታ ሁልጊዜ አንተ ኀያል አምባዬ ሁን፤ አንተ ኀያል አምባዬና ምሽጌ ስለ ሆንክ በትእዛዝህ አድነኝ።
አንተ በምትገለጥበት ጊዜ ጠላቶቼ ወደ ኋላ ይመለሳሉ፤ ተሰናክለውም ከፊትህ ይጠፋሉ።
እግዚአብሔር ሆይ! በዘመናት ሁሉ አንተ መጠጊያችን ነህ።