ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
መዝሙር 88:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሙታን መካከል ፈጽሞ እንደ ተተዉ፥ ተገድለው በመቃብር እንደ ተጋደሙ፥ ከእንግዲህ ፈጽሞ እንደማታስታውሳቸውና የአንተ እንክብካቤ ከእነርሱ እንደ ተቋረጠ ሰዎች መስዬአለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሙታን መካከል እንደ ተጣሉ፣ ተገድለው በመቃብር ውስጥ እንደ ተጋደሙ፣ አንተ ከእንግዲህ እንደማታስባቸው፣ ከእጅህም ወጥተው እንደ ተወገዱ ሆንሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቈጠርሁ፥ ረዳትም እንደሌለው ሰው ሆንሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ ሰማያት ክብርህን ጽድቅህንም ደግሞ በቅዱሳን ማኅበር ያመሰግናሉ። |
ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ፤ ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም መጒደል ጀመረ።
በእርሱ ላይ የተዛባ ፍርድ ተወስኖበት ተወሰደ፤ የወደፊትስ ሁኔታውን ማስተዋል የሚችል ማነው? ሆኖም ስለ ሕዝቤ መተላለፍ ተመታ፤ ከሕያዋንም ዓለም ተወገደ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የእስራኤል ሕዝብ እኮ ልክ እንደእነዚህ አጥንቶች ናቸው፤ እነርሱ ‘እነሆ፥ አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋ ቈርጠናል፤ የእኛ ጉዳይ አልቆለታል’ ይላሉ።