እባክህ ጸሎቴን ስማ! ጩኸቴንም አድምጥ!
ጸሎቴ በፊትህ ትድረስ፤ ጆሮህንም ወደ ጩኸቴ አዘንብል።
አቤቱ፥ የመድኃኒቴ አምላክ፥ በቀንና በሌሊት በፊትህ ጮኽሁ፥
“ምሕረትን ለዘለዓለም አንጻለሁ” ብለሃልና፥ ጽድቅህ በሰማይ ጸና።
“አንድ ሰው ባልንጀራውን መበደሉን የሚገልጥ ክስ ቀርቦበት በዚህ ቤተ መቅደስ ውስጥ ወደሚገኘው መሠዊያ አምጥተውት ከበደል ንጹሕ መሆኑን በመሐላ በሚያረጋግጥበት ጊዜ፥
ጎህ ከመቅደዱ በፊት ርዳታህን በመፈለግ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በገባህልኝም ቃል ተስፋ አደርጋለሁ።
ሆኖም አንተ በእስራኤል የተመሰገንክ፥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠህ የምትገዛ ቅዱስ አምላክ ነህ።
ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።
የእስረኞች መቃተት ወደ አንተ እንዲደርስ አድርግ፤ ሞት የተፈረደባቸውንም በታላቁ ኀይልህ አድናቸው።
ጌታዬ ሆይ! ማረኝ፤ ቀኑን ሁሉ ወደ አንተ እጸልያለሁ።
ለእርዳታ ጩኸቴን ባሰማም እንኳ አላዳምጥ አለኝ።