መዝሙር 83:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ አምላኬ ሆይ! እንደ ትቢያ፥ በነፋስም እንደሚወሰድ ገለባ በትናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላኬ ሆይ፤ በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዳ ትቢያ፣ በነፋስም ፊት እንዳለ ገለባ አድርጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግዚአብሔርን መስክ እንወርሳለን የሚሉትን። |
እነርሱ ገና እንደ በቀለና ሥር እንዳልሰደደ አዲስ ተክል ናቸው፤ እግዚአብሔር ነፋሱን ሲልክ ወዲያውኑ ይደርቃሉ፤ እንደ ገለባም በነው ይጠፋሉ።
“ድል አድራጊውን አነሣሥቶ ከምሥራቅ ያመጣ፥ እንዲያገለግለው የጠራው ማነው? ሕዝቦችን አሳልፎ ለእርሱ ይሰጣቸዋል። ነገሥታትንም ያስገዛለታል፤ በሰይፉ እንደ ትቢያ በፍላጻዎቹም እንደ ገለባ ይበታትናቸዋል።
“ ‘እኔ እግዚአብሔር እዚያ ያለሁ ብሆንም እንኳ ሁለቱን ሕዝቦች፥ ማለት ይሁዳንና እስራኤልን፥ እንዲሁም ምድራቸውን ጭምር የእናንተ አድርጋችሁ ለመውረስ አስባችሁ ነበር።
እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”