መዝሙር 82:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፤ የሕይወታችሁም ፍጻሜ እንደ ማንኛውም ምድራዊ ገዢ ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን እንደ ማንኛውም ሰው ትሞታላችሁ፤ እንደ ማንኛውም ገዥ ትወድቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እንደ ሰው ትሞታላችሁ፥ ከአለቆችም እንደ አንዱ ትወድቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌባል፥ አሞንም፥ አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤ |
ታዲያ ሊገድሉህ በሚመጡበት ጊዜ አሁንም ራስህን እንደ አምላክ ትቈጥር ይሆን? በገዳዮችህ እጅ ወድቀህ ስትገኝ ሰው እንጂ አምላክ ያለመሆንህ ይታወቃል።
የቱንም ያኽል ውሃ እየጠጣ ቢያድግ በዚህ ዐይነት ከፍተኛ ቁመት እስከ ደመና የሚደርስ ዛፍ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አይኖርም። ሟቾች በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው የሞት ፍርድ በእነርሱም ላይ ይደርሳል፤ ወደ ሙታን ዓለምም ይወርዳሉ።”