በሰላም ስለ መራቸው አልፈሩም፤ ነገር ግን ባሕሩ ተጥለቅልቆ ጠላቶቻቸውን አሰጠማቸው።
ያለ ሥጋት መራቸው፤ እነርሱም አልፈሩም፤ ጠላቶቻቸውን ግን ባሕር ዋጣቸው።
በተስፋም መራቸው አልፈሩምም፥ ጠላቶቻቸውንም ባሕር ደፈናቸው።
ጠላቶቻቸውን ግን ውሃው አሰጠማቸው፤ ከእነርሱ አንድ እንኳ በሕይወት የቀረ አልነበረም።
የግብጽን ንጉሥና ሠራዊቱን በቀይ ባሕር አሰጠመ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
ሙሴም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “አይዞአችሁ አትፍሩ! ባላችሁበት ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር እናንተን ለማዳን የሚያደርገውን ዛሬ ታያላችሁ፤ እነዚህን ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያን ዳግመኛ አታዩአቸውም።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ወደ እኔ የምትጮኸው ለምንድን ነው? ይልቅስ ሰዎቹን ወደ ፊት እንዲጓዙ ንገራቸው፤
ነገር ግን አምላክ ሆይ፥ ከአንተ በተገኘው በአንድ ትንፋሽ ግብጻውያን ሁሉ ሰጠሙ፤ በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደ ተጣለ ብረት ሆነው ቀሩ።
ሙሴም የዐማቱን ምክር ሁሉ ተቀብሎ በሥራ ላይ አዋለው።
እስራኤላውያን በደረቅ ምድር እንደሚሻገሩ ሆነው ቀይ ባሕርን የተሻገሩት በእምነት ነው፤ ግብጻውያን ግን እንዲሁ ለማድረግ በሞከሩ ጊዜ ሁሉም ሰጠሙ።