አንተ ለምድር ዳርቻን ወሰንህ፤ ክረምትና በጋ እንዲፈራረቁ አደረግህ።
የምድርን ዳርቻ ሁሉ የወሰንህ አንተ ነህ፤ በጋውንም ክረምቱንም አንተ ሠራህ።
አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ አረጋገጥህ፥ በጋንም ክረምትንም አንተ ሠራህ።
ምድር እስካለች ድረስ፥ ለመዝራትና ለማጨድ፥ ለብርድና ለሙቀት፥ ለበጋና ለክረምት፥ ለቀንና ለሌሊት የማያቋርጥ ጊዜ ይኖራል።”
ዓለም ምን ያኽል ትልቅ እንደ ሆነች ማወቅ ትችላለህን? እስቲ ይህን ሁሉ ታውቅ እንደ ሆነ ንገረኝ።
ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”
እርሱ የሰውን ዘር ሁሉ ከአንድ ሰው ፈጠረ፤ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩም አደረገ፤ የተወሰኑ ዘመኖችንና የሚኖሩባቸውንም ቦታዎች መደበላቸው።
ልዑል እግዚአብሔር ለሕዝቡ ርስታቸውን ባከፋፈለ ጊዜ፥ የሰውን ዘር በለያየ ጊዜ፥ እንደ እስራኤል ልጆች ቊጥር ብዛት፥ ለሕዝቡ ድንበርን ሠራላቸው።