La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 73:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህን ለመረዳት ኅሊናዬን አነቃሁ፤ ነገር ግን በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህን ነገር ለመረዳት በሞከርሁ ጊዜ፣ አድካሚ ተግባር መስሎ ታየኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቀኑ የአ​ንተ ነው፥ ሌሊ​ቱም የአ​ንተ ነው፤ አንተ ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን ፈጠ​ርህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 73:16
10 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ፥ ሰዎችንና እንስሶችን ከአደጋ ታድናለህ፤ ጽድቅህ እንደ ተራራዎች እጅግ ከፍ ያለ ነው፤ ፍርድህም እንደ ባሕር ጥልቅ ነው።


ሰው ከጥላም የተሻለ አይደለም፤ በከንቱ ይደክማል፤ ሀብትን ያከማቻል፤ ነገር ግን ማን እንደሚጠቀምበት አያውቅም።


መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤ ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤ ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም።


ብሩህና ጥቊር ደመና ዙሪያውን ከበውታል፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።


ስለዚህ ጥበብንና ዕውቀትን፥ እብደትንና ሞኝነትን ዐውቅ ዘንድ ኅሊናዬን አተጋለሁ፤ ይህም ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ሆኖ አገኘሁት።


ሰው በምርምር ብዛትም እግዚአብሔር የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ማወቅ እንደማይችል አረጋገጥኩ፤ ሰው ብዙ ነገር መርምሮ ለማወቅ የቱንም ያኽል ቢደክም አንዳች ነገር ማግኘት አይችልም፤ በእርግጥ ጥበበኞች ሰዎች “ይህንን እናውቃለን” ለማለት ይደፍሩ ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የሚያውቁት ነገር የለም።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ ዕውቀትም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ የማይመረመር፥ መንገዱም የማይታወቅ ነው።