ሐሳቤን በቅንነት መጠበቄና በደልንም ከመሥራት መቈጠቤ ምን ጠቀመኝ?
ለካ ልቤን ንጹሕ ያደረግሁት በከንቱ ነው፤ እጄንም በየዋህነት የታጠብሁት በከንቱ ኖሯል!
እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።
አንተ ባሕርን በኀይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቡን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
‘እናመልከው ዘንድ ሁሉን ቻይ አምላክ ማነው? ወደ እርሱስ መጸለይ ምን ይጠቅመናል?’ ይላሉ።
‘እግዚአብሔርን ማስደሰት፥ ለሰው ምንም አይጠቅመውም’ ይላል።
‘ኃጢአት ባልሠራ ምን እጠቀማለሁ? ምንስ አተርፋለሁ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።
ሮሮዬን ልርሳ፥ ፊቴንም ማጥቈር ትቼ ፈገግታ ላሳይ ብል፥
እንግዲህ በደለኛ ሆኜ ከተቈጠርኩ፥ በከንቱ መድከሜ ለምንድን ነው?
ይህም ሁሉ ሆኖ አንተ ወደ አዘቅት ትጥለኛለህ፤ የገዛ ልብሴ እንኳ ይጸየፈኛል።
ይህን ማድረግ የሚችል፥ እጆቹ ከክፉ ሥራና ልቡም ከክፉ ሐሳብ ንጹሓን የሆኑ፥ ጣዖትን የማያመልክ፥ ዋሽቶ የማይምል ነው።
እግዚአብሔር ሆይ! ንጹሕነቴን ለማሳየት እጆቼን እታጠባለሁ፤ መሠዊያህንም በመዞር አንተን አመልካለሁ።
አምላክ ሆይ! ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ፤ አዲስና የጸና መንፈስን ስጠኝ።
እናንተ ‘እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዞቹን መጠበቅና እንደ ሐዘንተኞች በሠራዊት አምላክ ፊት መመላለስ ምን ይጠቅመናል?
ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል፤ እናንተ ኃጢአተኞች! እጆቻችሁን አጽዱ፤ እናንተ ወላዋዮች! ልባችሁን አጥሩ።