መዝሙር 72:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንጉሡ ሣሩ በታጨደ መስክ ላይ እንደሚዘንብ ዝናብ፥ በምድርም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ ይወርዳል፤ እንደ ካፊያም ምድርን ያረሰርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይውረድ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም ትዕቢት ያዛቸው፤ ኀጢአታቸውንና በደላቸውን ተጐናጸፉአት። |
ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትሰጣለህ፤ ወጣ ገባውን ታስተካክላለህ፤ ዐፈሩንም በካፊያ ታለሰልሳለህ፤ ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ።
ከዚያን በኋላ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ ስለዚህም አራሙቻ እንዲበቅልበት፥ በኲርንቺትና በእሾኽ እንዲሸፈን አደርጋለሁ፤ ዝናብም እንዳያዘንብበት ደመናን አዛለሁ።”
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
የናምሩድ ግዛት የነበረችውንም በሠራዊታቸው ኀይል አሦርን ድል ነሥተው ይይዛሉ፤ አሦራውያን አገራችንን ቢወሩና ድንበራችንን ቢረግጡ እርሱ ከእጃቸው ያድነናል።