La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 70:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ ሐሴትም ያድርጉ፤ ማዳንህን የሚወዱ ሁሉ ዘወትር “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን፣ ሐሤት ያድርጉ፤ በአንተም ደስም ይበላቸው፤ ማዳንህን የሚወድዱ ሁሉ ሁልጊዜ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ይበል!” ይበሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እሰይ እሰይ የሚሉኝ አፍረው ወዲያው ወደ ኋላቸው ይመለሱ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አም​ላኬ ከኃ​ጥ​ኣን እጅ፥ ከዐ​መ​ፀ​ኛና ከግ​ፈ​ኛም እጅ አድ​ነኝ።

Ver Capítulo



መዝሙር 70:4
8 Referencias Cruzadas  

ድል ማድረጌ የሚያስደስታቸው ሁሉ ደስ ይበላቸው፤ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው! ለአገልጋዩ ሁኔታዎች ሁሉ ሲሳኩለት እግዚአብሔር ደስ ይለዋል!” ይበሉ።


አንተን የሚፈልጉ ሁሉ ግን ደስ ይበላቸው፥ ሐሴትም ያድርጉ፤ ያንተን ማዳን የሚወዱ ዘወትር፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነው!” ይበሉ።


በአንተ ከለላ ሥር ያሉ ሁሉ ይደሰቱ፤ ለዘለዓለምም እልል ይበሉ የአንተን ስም የሚወዱትን ሁሉ በደስታም እንዲፈነድቁ ከልላቸው።


እግዚአብሔር ስላደረገው ነገር ጻድቃን ሁሉ ደስ ይበላችሁ! ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ!


እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ ሁለንተናዬም በአምላኬ ሐሴትን ያደርጋል፤ የአበባ አክሊል በራሱ ላይ እንደሚያደርግ ሙሽራ፥ በጌጣጌጥም እንዳሸበረቀች ሙሽሪት አድርጎ፥ የመዳንን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።


እግዚአብሔር በተስፋ ለሚጠባበቁትና እርሱን ለሚፈልጉ መልካም ነው።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ትጮኻላችሁም፤ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተ ታዝናላችሁ፤ ነገር ግን ሐዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።