ኃጢአተኞች በደልን ይፀንሳሉ፤ ተንኰልን ያረግዛሉ፤ ውሸትን ይወልዳሉ።
ክፋትን እያማጠ ያለ ሰው፣ ቅጥፈትን አርግዞ፣ ሐሰትን ይወልዳል።
የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።
እነሆ፥ ዐመፀኛ በዐመፁ ተጨነቀ፤ ጭንቅን ፀነሰ፤ ኀጢአትንም ወለደ።
“ሰዎችን ሲጨቊን የኖረ ክፉ ሰው ዕድሜ ልኩን ሲሠቃይ ይኖራል።
እንደዚህ ያሉ ሰዎች ተንኰልን ያቅዳሉ፤ ችግርንም ይወልዳሉ፤ ልባቸውም በአታላይነት የተሞላ ነው።”
ገለባን ፀንሳ እብቅ እንደምትወልድ እስትንፋሳችሁ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያችኋል።
“ተከታታይ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤ ፍላጻዎቼን ሁሉ በእነርሱ ላይ እጨርሳለሁ።
ከዚህ በኋላ ምኞት ስትፀንስ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ስታድግ ሞትን ትወልዳለች።