በፊታቸው የተዘረጋው ማእድ ወጥመድና የሚመገቡትም ምግብ የመውደቂያቸውና የመጥፊያቸው ምክንያት ይሁን።
በፊታቸው ያለው ማእድ ወጥመድ ይሁንባቸው፤ ለማኅበራቸውም እንቅፋት ይሁን።
ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።
ዕውቀት የጐደላቸው ሰዎች ከጥበብ በመራቃቸው ምክንያት ይሞታሉ፤ ሞኞችም ከቸልተኛነታቸው የተነሣ ይጠፋሉ።
ባታዳምጡ፥ ለስሜም ክብር ለመስጠት ቃሌን በልባችሁ ባታኖሩት መርገም እልክባችኋለሁ፤ በረከታችሁንም ወደ ርግማን እለውጣለሁ፤ እኔን ማክበር በልባችሁ ውስጥ ስለሌለ በእርግጥ ይህን ሁሉ አደርግባችኋለሁ።
“የእህል ሰብልህና ቡሃቃህ የተረገመ ይሆናል።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።
ደግሞም፥ “እነሆ! ሰዎችን የሚያሰናክል ድንጋይ፤ እነሆ! ሰዎችን አደናቅፎ የሚጥል አለት” ይላል። እነርሱ ቃሉን ባለማመናቸው ይሰናከላሉ፤ አስቀድመውም ለዚህ የተመደቡ ናቸው።