መዝሙር 69:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቆሚያ ስፍራ ስለ አጣሁ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ለመስረግ ተቃርቤአለሁ፤ በጥልቅ ውሃ ውስጥ እገኛለሁ፤ ውሃ ሙላት ሊያሰጥመኝ ተቃርቦአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግር መቆሚያ በሌለው፣ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ሰጥሜአለሁ፤ ወደ ጥልቅ ውሃ ገባሁ፤ ሞገዱም አሰጠመኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደርሶብኛልና አድነኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ፥ ይጐስቍሉም፥ ክፉንም የሚመክሩብኝ ወደኋላቸው ይመለሱ፥ ይፈሩም። |
ይኸውም በይሁዳ ቤተ መንግሥት የቀሩት ሴቶች ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ባለ ሥልጣኖች ተወስደው በሚሄዱበት ጊዜ እንዲህ ይሉሃል፦ ‘የቅርብ ወዳጆችህ አስተውሃል፤ እነርሱም በአንተ ላይ ሠልጥነውብሃል፤ አሁን ግን እግርህ ማጥ ውስጥ ስለ ገባ ጥለውህ ሄደዋል።’ ”
ስለዚህም እኔን ይዘው በቤተ መንግሥቱ አደባባይ በሚገኘው ወደ ንጉሥ ልጅ ወደ መልክያ የውሃ ጒድጓድ ውስጥ በገመድ ቊልቊል በመልቀቅ ወደ ታች አወረዱኝ፤ በጒድጓዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውሃ አልነበረበትም፤ እኔም በጭቃው ውስጥ ሰመጥሁ።
ወደ ተራራዎች ሥር ወረድኩ፤ ከዚያ በታች ባለው ምድርም ውስጥ ለዘለዓለም ሊዘጋብኝ ነበር፤ አንተ ግን እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እኔን ከጥልቁ ውሃ አውጥተህ ሕይወቴን ታድናለህ።