መዝሙር 66:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ባሕሩን ወደ ደረቅ መሬት ለውጦአል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ወንዙን በእግር ተሻግረዋል፤ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሕሩን የብስ አደረገው፤ ወንዙን በእግር ተሻገሩ፤ ኑ፣ በርሱ ደስ ይበለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሕርን የብስ አደረጋት፥ ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፥ በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር አምላካችንም ይባርከናል፥ የምድርም ዳርቻ ሁሉ ይፈሩታል። |
ውሃው መውረዱን አቆመ፤ በጻርታን አጠገብ አዳም ተብላ እስከምትጠራው ከተማ ድረስ ተከመረ፤ ወደ ሙት ባሕር ይፈስ የነበረውም ጐርፍ በፍጹም ተቋረጠ፤ ስለዚህም ሕዝቡ ወደ ማዶ ወደ ኢያሪኮ ተሻገሩ።
ሕዝቡ በደረቅ ምድር እየተራመዱ በሚሻገሩበት ጊዜ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እስካበቁ ድረስ በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል በደረቅ ምድር ላይ ቆመው ነበር።