መዝሙር 65:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዝናብን በማዝነብ ምድርን ትጐበኛለህ፤ ፍሬያማ በማድረግ ታበለጽጋታለህ፤ ምንጮችህን በውሃ ትሞላለህ፤ ለምድርም ሰብልን ትሰጣለህ። ይህንንም የምታደርገው እንዲህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርን ትጐበኛለህ፤ ታጠጣለህም፤ እጅግ ታበለጥጋታለህም። ለሰዎች እህልን ይለግሱ ዘንድ፣ የእግዚአብሔር ወንዞች ውሃን የተሞሉ ናቸው፤ አንተ እንዲህ እንዲሆን ወስነሃልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተኣምራትህ የተነሣ በምድር ዳርቻ የሚኖሩ ይፈራሉ፥ የጥዋትንና የማታን መውጫዎች ደስ ታሰኛቸዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥ ለእግሮቼም ሁከትን አልሰጠም። |
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ለማግኘት በብርቱ እናፍቃለሁ፤ ሁለንተናዬ አንተን ይመኛል፤ ውሃ በማጣት ደርቆ እንደ ተሰነጣጠቀ መሬት ነፍሴ አንተን ተጠማች።
“በደሴቶች የሚኖሩ ሕዝቦች እኔ ያደረግኹትን ሁሉ አይተዋል፤ ስለዚህም እጅግ ደንግጠው ተንቀጥቅጠዋል፤ በአንድነትም ተሰብስበው ወደ እኔ መጥተዋል።
ከአሕዛብ አማልክት መካከል አንዱ እንኳ ዝናብ ማዝነብ አይችልም፤ ሰማይም በራሱ ፈቃድ ካፊያ አያወርድም፤ እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! ይህን ሁሉ የምታደርግ አንተ ስለ ሆንክ እኛ ተስፋ የምናደርገው በአንተ ነው።
የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በወቅቱ የምሰጣችሁ፥ የመከርንም ወራት በየዓመቱ የማመላልስላችሁ እኔ ነኝ፤ እናንተ ግን እኔን ማክበርን ተዋችሁ።
እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።
ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”
ናዖሚ በሞአብ አገር ሳለች፥ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት እንዳደረገላቸውና ብዙ መከር እንደ ሰጣቸው ሰማች፤ ስለዚህ ከሁለቱ ምራቶችዋ ጋር ከሞአብ ወደ እስራኤል ለመመለስ ተነሣች።