እንዲሁም ከበረትህ ኰርማዎችን፥ ከጒሮኖህም አውራ ፍየሎችን ልወስድብህ አልፈልግም።
እኔ ግን ኰርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጕረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤
ከቤትህ ፍሪዳን ከመንጋህም አውራ ፍየልን አልወስድም፥
ከኀጢአቴ ፊትህን መልስ፥ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ።
ስለዚህ “ስለ እኔ በተጻፈው የሕግ መጽሐፍ መሠረት እነሆ እኔ መጥቻለሁ።
ይህም የተሟላ ዕድገት ያለው ኰርማ ወይም ወይፈን ከመሠዋት ይልቅ እግዚአብሔርን የበለጠ ያስደስተዋል።
ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌሎችንም ነገሮች ለሰው ሁሉ የሚሰጥ እርሱ ስለ ሆነ ምንም ነገር አይጐድለውም፤ የሰውም ርዳታ አያስፈልገውም።