“ጌታ ሆይ! መጨረሻዬንና የቀኖቼን ብዛት እንዳውቅ አድርገኝ፤ ዕድሜዬም ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ ንገረኝ።”
“እግዚአብሔር ሆይ፤ የሕይወቴን ፍጻሜ፣ የዘመኔንም ቍጥር አስታውቀኝ፤ ዐላፊ ጠፊ መሆኑንም ልረዳ።
ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ፥ ከማሰቤም የተነሣ እሳት ነደደ፥ በአንደበቴም ተናገርሁ፦
መታመኛው የእግዚአብሔር ስም የሆነ፥ ወደ ከንቱ ነገር፥ ወደ ቍጣና ወደ ሐሰትም፥ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።
“ምነው፥ በሙታን ዓለም ብትሰውረኝ! ቊጣህም እስከሚያልፍ ብትሸሽገኝ! የቀጠሮም ቀን ወስነህ ብታስበኝ!
እግዚአብሔር ከምን እንደ ተፈጠርን ያውቃል፤ ዐፈር መሆናችንንም ያስታውሳል።
እኔ አገልጋይህ እስከ መቼ ልቈይ? የሚያሳድዱኝንስ የምትቀጣቸው መቼ ነው?
ጥበበኞች ለመሆን እንድንችል ዕድሜአችን ምን ያኽል አጭር እንደ ሆነ አስተምረን።