ያዘንኩትም ለወዳጅ ወይም ለወንድም የሚታዘነውን ያኽል ነው፤ እናቱ የሞተችበት ሰው የሚያዝነውን ያኽል ራሴን ዝቅ አድርጌ አለቀስኩ።
ለወዳጄ ወይም ለወንድሜ እንደማደርግ፣ እየተንቈራጠጥሁ አለቀስሁ፤ ለእናቴም እንደማለቅስ፣ በሐዘን ዐንገቴን ደፋሁ።
ለወዳጄና ለወንድሜ እንደማደርግ አደረግሁ፥ ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ ዝቅ አደረግሁ።
ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።
ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤ ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
ነገር ግን ጳውሎስ፥ “ሁላችንም እዚህ ነን! ስለዚህ በራስህ ላይ ጒዳት አታድርስ!” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።