መዝሙር 30:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ሞገስን በሰጠኸኝ ጊዜ እንደማይነቃንቅ ተራራ አበረታኸኝ፤ ፊትህን በሰወርክ ጊዜ ግን ተስፋ ቈረጥኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በአንተ ሞገስ፣ ተራሮቼ ጸኑ፣ ፊትህን በሰወርህ ጊዜ ግን፣ ውስጤ ታወከ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በደስታዬ፦ ለዘለዓለም አልታወክም አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በትድግናህ ደስ ይለኛል፤ ሐሴትም አደርጋለሁ። መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና። |
እግዚአብሔር ሆይ! መንፈሴ ስለ ዛለብኝ ፈጥነህ መልስ ስጠኝ! ፊትህን ከእኔ አትሰውርብኝ! አለበለዚያ ወደ ጥልቁ ጒድጓድ እንደሚወርዱት ሰዎች እሆናለሁ።
እነርሱ ምድርን የወረሱት በሰይፋቸው አይደለም፤ ድል አድርገው የወሰዱትም በራሳቸው ኀይል አይደለም፤ ይህን ሁሉ ያደረጉት አንተ ስለ ወደድካቸውና ከእነርሱም ጋር በመሆን በኀይልህና በብርታትህ ስለ ረዳሃቸው ነው።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።