መዝሙር 30:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዋስትና እንዳለኝ ስላወቅሁ “ከቶ አልሸነፍም” አልኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በተረጋጋሁ ጊዜ፣ “ከቶ አልናወጥም” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣው ለጥቂት ጊዜ ነው፥ ሞገሱ ግን ለሕይወት ዘመን፥ ልቅሶ ማታ ይመጣል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንቱን ነገር የሚጠብቀውን ሁሉ ሁልጊዜ ጠላህ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ታመንሁ። |
ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ ንጹሕ ሰዎችን ለመጒዳት ጉቦ የማይቀበል፥ እነዚህን ነገሮች የሚያደርግ ሰው ከቶ አይናወጥም። በሰላም ይኖራል እንጂ ከቶ አይናወጥም።
‘እኔ ለዘለዓለም ንግሥት ሆኜ እኖራለሁ’ አልሽ፤ ስላደረግሽው ድርጊት ምንም አላሰብሽም፤ የተግባርሽም ውጤት ምን እንደሚሆን አላስተዋልሽም።
ንጉሡም እንዲህ አለ፦ “ይህችን ታላቋን ባቢሎን የነገሥታት መኖሪያና ዋና ከተማ ሆና የእኔ ክብርና ግርማ እንዲገለጥባት በሥልጣኔ የሠራኋት እኔ አይደለሁምን?”
ከዚህም በኋላ ራሴን፦ እነሆ፥ ለብዙ ዓመት የሚበቃህ ብዙ ሀብት አለህ፤ እንግዲህ ዕረፍት በማድረግ ተዝናና! ብላ! ጠጣ! ደስ ይበልህ! እለዋለሁ’ አለ።
ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።