እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ጮክ ብዬ ስጣራ ስማኝ! ምሕረትን አድርግልኝ፤ ጸሎቴንም ስማ!
እግዚአብሔር ሆይ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ ስጮኽ ስማኝ፤ ራራልኝ፤ ስማኝም።
አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ፥ ማረኝና አድምጠኝ።
እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤ ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።
እግዚአብሔርን እንዲህ እለዋለሁ፦ በእኔ ላይ ያለህን ቅርታ ግለጥልኝ እንጂ አትፍረድብኝ!
እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ አድምጠኝና መልስ ስጠኝ፤ የሞት እንቅልፍ አንቀላፍቼ እንዳልወድቅ ብርታቱን ስጠኝ።
አንተ ሐዘኔን ወደ ደስታ ለወጥክልኝ፤ ትካዜዬን ከእኔ አስወገድክልኝ፤ የማቅ ልብሴን አውልቀህ ደስታን አለበስከኝ።
ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
አንተ የእውነት አምላክ ነህ፤ እባክህን ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ! እኔ በጣም በጭንቀት ላይ ነበርኩ አንተ ግን ነጻ አወጣኸኝ፤ አሁንም ራራልኝና ጸሎቴን ስማ።
ንጉሤና አምላኬ ሆይ! ወደ አንተ ስለምጸልይ ለእርዳታ የምጮኸውን ጩኸት አድምጥ።