መዝሙር 26:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በበኩሌ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት እኖራለሁ፤ ምሕረትን አድርግልኝ፤ አድነኝም! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ግን በተአማኒ ሕይወት እጓዛለሁ፤ አድነኝ፤ ምሕረትንም አድርግልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን በቅንነት ሄጃለሁ፥ አድነኝ ማረኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ። |
ሌዋውያኑም በሕጉ መሠረት ራሳቸውን አንጽተው የሰንበት ቀን በቅድስና የተጠበቀች መሆንዋን ለማረጋገጥ የቅጽር በሮቹን እንዲቈጣጠሩ አዘዝኳቸው። እግዚአብሔር ሆይ! ስለዚህም ሁሉ እንድታስበኝና ስለ ጽኑ ፍቅርህም እንድትታደገኝ እለምንሃለሁ።
መሥዋዕት የሚቃጠልበትን ማገዶ በተወሰነው ክፍለ ጊዜ ሁሉ ማቅረብ የሚቻልበትን ሁኔታ አደራጀሁ፤ ሰዎቹም ከሚሰበስቡት ሰብል ሁሉ ከእህሉም ሆነ ከፍራፍሬው በመጀመሪያ የደረሰውን እንዴት ማቅረብ እንደሚገባቸው አዘጋጀሁ። አምላኬ ሆይ! ይህን ሁሉ አስብ፤ ይህን በማድረጌም ቸርነት አድርግልኝ።
ከእኔ በፊት የሕዝብ ገዢ ሆኖ የተሾመው ሁሉ በሕዝቡ ላይ ከባድ ሸክም በመሆን፥ በየቀኑ ለምግብና ለመጠጥ የሚሆን አርባ ብር ያስከፍላቸው ነበር፤ የገዢዎቹም አገልጋዮች እንኳ በሕዝቡ ላይ ሠልጥነውባቸው ይጨቊኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንደዚያ አላደረግሁም።
ዑፅ ተብላ በምትጠራ አገር ኢዮብ የሚባል አንድ ሰው ነበር፤ እርሱም ከክፉ ነገር ሁሉ ርቆ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ምንም ነውር የሌለበት፥ ቅን ሰው ነበር።
በእናንተ በአማኞች መካከል በነበርንበት ጊዜ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ሕይወት እንደ ኖርን እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክር ነው፤
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።