መዝሙር 22:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀድሞ አባቶቻችን በአንተ ተማመኑ፤ በአንተም ስለ ተማመኑ አዳንካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፤ ተማመኑብህ፤ አንተም ታደግሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ውዳሴዎች የምትኖር አንተ ግን ቅዱስ ነህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኩዝህ እነርሱ ያጽናኑኛል። |
ሰውየውም፥ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ከእግዚአብሔርም ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃል፤ ስለዚህ ስምህ ‘እስራኤል’ ይባላል” አለው።
ከእነርሱም ጋር እምቢልታ የሚነፉ አንድ መቶ ኻያ ካህናት ነበሩ፤ እነዚህ መዘምራን ሁሉ በመለከት፥ በጸናጽል፥ በበገናና በሌሎችም የሙዚቃ መሣሪያዎች እየታጀቡ፦ “ቸር ስለ ሆነ፥ ፍቅሩም ዘለዓለማዊ ስለ ሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ” በማለት በአንድ ድምፅ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበር። በዚህ ጊዜ በድንገት የእግዚአብሔርን ክብር የሚገልጥ አንጸባራቂ ብርሃን የሞላበት ደመና የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ስለ ሞላው ካህናቱ የአምልኮ አገልግሎታቸውን ሊያከናውኑ አልቻሉም።
እግዚአብሔር በእንዴት ያለ ታላቅ ኀይል ግብጻውያንን እንዳሸነፈ እስራኤላውያን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርና በአገልጋዩ በሙሴ አመኑ።