መዝሙር 22:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የጽድቅ ሥራውን በማወጅ “እግዚአብሔር ሕዝቡን አዳነ” ብለው ገና ላልተወለዱ ሰዎች ይናገራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገና ላልተወለደ ሕዝብ፣ ጽድቁን ይነግራሉ፤ እርሱ ይህን አድርጓልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትውልድ ይገዛለታል፥ የሚመጣው ትውልድ ስለ ጌታ ይነገረዋል፥ |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይሁን እንጂ በሕማም አደቀው ዘንድ የእኔ ፈቃድ ነበር፤ ሕይወቱን የበደል መሥዋዕት አድርጎ በሚያቀርብበት ጊዜ ዘመኑ ተራዝሞ ብዙ ትውልድ ያያል፤ በእርሱም አማካይነት የእኔ ፈቃድ ይፈጸማል።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!
ቀና ብለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ተመልከቺ! ሁላቸውም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽም በሞግዚቶቻቸው ክንድ ሆነው ወደ አንቺ ይመጣሉ።
ጻድቅ በእምነት ሕይወትን ያገኛል ተብሎ ተጽፎአል፤ የእግዚአብሔር ጽድቅም በሥራ ስለ ታየ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻው ሰው የሚጸድቀው በእምነት ነው።