መዝሙር 17:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ለርኅራኄ ልባቸውን ዘግተዋል፤ አፋቸውም ትዕቢትን ይናገራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደንዳና ልባቸውን ደፈኑት፤ በአፋቸውም ትዕቢት ይናገራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ፥ በአፋቸውም ትንቢትን ተናገሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ። |
ንጉሡም “ለመሆኑ እግዚአብሔር ማን ነው? የእርሱንስ ትእዛዝ ሰምቼ እስራኤልን የምለቀው ለምንድን ነው? እኔ እግዚአብሔርን አላውቅም፤ እስራኤልንም አለቅም” አለ።
ቀጥሎም “እንዳያዩ፥ እንዳይሰሙና እንዳያስተውሉ በዓይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸው አስተውለው ወደ እኔ ተመልሰው እንዳይፈወሱ ይህን ሕዝብ ልቡ የደነደነ፥ ጆሮው የተደፈነ፥ ዐይኑም የተጨፈነ እንዲሆን አድርግ” አለኝ።
የእዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸው ተደፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተጨፍነዋል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው ተመልክተው፥ በጆሮአቸውም ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና በፈወስኳቸው ነበር።’
የእነዚህ ሰዎች ልብ ደንድኖአል፤ ጆሮአቸውም ተጨፍኖአል፤ ዐይናቸውም ተዘግቶአል፤ እንዲህስ ባይሆን ኖሮ፥ በዐይናቸው አይተው፥ በጆሮአቸው ሰምተው፥ በልባቸውም አስተውለው፥ ወደ እኔ በተመለሱና እኔም በፈወስኩአቸው ነበር።’
በስሕተት ከሚኖሩት ሰዎች መካከል አምልጠው ከመጡ ገና ብዙ ያልቈዩትን ሰዎች ከንቱ የሆነ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወትና በሴሰኛነት በማባበል ያታልሉአቸዋል።
እስቲ በመታበይ አትጓደዱ፤ የትምክሕት ንግግራችሁንም አስወግዱ፤ እግዚአብሔር አምላክ ሁሉን ያውቃል፤ ሕዝብ የሚሠራውንም ሁሉ በፍርድ ይመዝናል።