ይህን ሁሉ ለሌሎች ሕዝቦች አላደረገም፤ እነርሱ ሕጉንም አያውቁም። እግዚአብሔር ይመስገን!
ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤ እነርሱም ፍርዱን አላወቁም። ሃሌ ሉያ።
ለሌሎች አሕዛብ ሁሉ እንዲህ አላደረገም፥ ፍርዱንም አልገለጠላቸውም። ሃሌ ሉያ።
ከእግዚአብሔር የሚገለጥ መመሪያ ባይኖር ሕዝብ መረን ይለቀቃል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያከብር ሰው ግን የተባረከ ነው።
ባለፉት ዘመኖች ሕዝቦች ሁሉ በገዛ ራሳቸው መንገድ እንዲሄዱ እግዚአብሔር ትቶአቸዋል፤
ዐይናቸውን እንድትከፍትላቸውና ከጨለማ ወደ ብርሃን እንድታወጣቸው ከሰይጣንም ግዛት ወደ እግዚአብሔር እንድትመልሳቸው አደርግሃለሁ፤ እነርሱም በእኔ በማመናቸው ምክንያት የኃጢአታቸውን ይቅርታ ያገኛሉ፤ በተመረጡት መካከልም ርስትን ይካፈላሉ።’
ንጉሥ አግሪጳ ሆይ! ነቢያትን ታምን የለምን? እንደምታምን ዐውቃለሁ።”
እናንተ ከእስራኤል ማኅበረሰብ ግንኙነት የሌላችሁ፥ ለተስፋው ቃል ኪዳን እንግዶች የሆናችሁ፥ በዚህ ዓለምም አንዳች ተስፋ የሌላችሁ፥ ያለ እግዚአብሔር የምትኖሩ፥ ከክርስቶስም የተለያችሁ እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።
ቀድሞ እናንተ በጨለማ ውስጥ ትኖሩ ነበር፤ አሁን ግን የጌታ ስለ ሆናችሁ ብርሃን ናችሁ ስለዚህ በብርሃን እንደሚኖሩ ሰዎች ተመላለሱ።