Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 29:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከእግዚአብሔር የሚገለጥ መመሪያ ባይኖር ሕዝብ መረን ይለቀቃል፤ የእግዚአብሔርን ሕግ የሚያከብር ሰው ግን የተባረከ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ራእይ በሌለበት ሕዝብ መረን ይሆናል፤ ሕግን የሚጠብቅ ግን የተባረከ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ራእይ ከሌለ ሕዝብ ከመስመር ይወጣል፥ ሕግን የሚጠብቅ ግን ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 29:18
21 Referencias Cruzadas  

የይሁዳ ንጉሥ አካዝ በሀገሩ ላይ ክፉ ነገርን ስላስፋፋና ለእግዚአብሔር የነበረውን ታማኝነት ስላጐደለ፥ እግዚአብሔር በይሁዳ ላይ ችግርና መከራ እንዲወርድ ፈቀደ።


ፍትሕን የሚከተሉና ዘወትር ትክክለኛ የሆነውን ነገር የሚያደርጉ፥ እንዴት የተባረኩ ናቸው?


በአካሄዳቸው ነቀፋ የሌለባቸው፥ በእግዚአብሔር ሕግ መሠረት የሚኖሩ ሰዎች የተባረኩ ናቸው።


ትእዛዞቹን የሚጠብቁ፥ በሙሉ ልባቸውም የሚፈልጉት፥ የተባረኩ ናቸው።


እንዲሁም አገልጋይህ በእነርሱ ይመከራል፤ እነርሱንም በመጠበቅ ታላቅ ዋጋ ያገኛል።


ከእንግዲህ ወዲህ ተአምራት አይኖሩም፤ ነቢያትም አይኖሩም፤ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ እንደሚቈይ ከእኛ መካከል ማን ያውቃል?


አሮን ሕዝቡን በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ መረን እንደ ለቀቃቸው ሙሴ ተመለከተ።


ትእዛዝን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚንቅ ግን ይጠፋል።


አንድን አገልጋይ በቃል በመገሠጽ ብቻ ለማረም አይቻልም፤ የምትለው ነገር ቢገባው እንኳ አይታዘዝም።


“ልጆቼ ሆይ! አድምጡኝ መንገዴን የሚከተሉ ይደሰታሉ።


ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።


ሕዝቡ ግን እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ባያቸው ጊዜ አዘነላቸው።


ኢየሱስ ግን “የተባረኩስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው በሥራ ላይ የሚያውሉት ናቸው፤” አላት።


ይህን ነገር ብታውቁና በሥራ ላይ ብታውሉት የተባረካችሁ ናችሁ።


ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹም ሕግ መርምሮ በእርሱ የሚጸና፥ እርሱንም ሰምቶ መርሳት ሳይሆን፥ በሥራ ላይ የሚያውለው ሰው በሥራው የተባረከ ይሆናል።


ከሕይወት ዛፍ ፍሬ ለመብላትና በደጃፎችዋም ወደ ከተማይቱ ለመግባት መብት እንዲኖራቸው ልብሳቸውን ያጠቡ የተባረኩ ናቸው።


ወጣቱ ሳሙኤል በዔሊ የአመራር ሥልጣን ሥር ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፤ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ዘወትር አይሰማም ነበር፤ ራእይም አይታይም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos