እግዚአብሔር ሆይ! ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።
ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
እንግዲያውስ መጥፎ ነገር ከማውራትና ሐሰት ከመናገር ተቈጠቡ።
እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።
አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልኩ፤ መልካም ስለ ሆነ ነገር እንኳ አልተናገርኩም፤ ነገር ግን ሥቃዬ ከበፊት ይልቅ እየባሰ ሄደ።
አንደበቴ በአንተ ምስጋና የተሞላ ነው፤ ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ። ድምፄንም ከፍ አድርጌ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ።
በሰው ላይ እምነትህን አትጣል፤ በቅርብ ወዳጅህም አትተማመን፤ አቅፈሃት ለምትተኛው ሚስትህ የምትናገረው ቃል እንኳ ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።
አንደበቱን ሳይቈጣጠር እግዚአብሔርን አመልካለሁ የሚል ሰው ራሱን ያታልላል፤ የእርሱም አምልኮ ከንቱ ነው።
እኛ ሁላችን ብዙ ጊዜ እንሳሳታለን፤ በንግግሩ የማይሳሳት እርሱ ሰውነቱን መቈጣጠር የሚችል ፍጹም ሰው ነው።