በዙሪያዬ ሁሉ ትገኛለህ፤ በኀይልህም ትጠብቀኛለህ።
አንተ ከኋላም ከፊትም ዙሪያዬን ከለልኸኝ፤ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
ከኋላና ከፊት ጠበቅኸኝ፥ እጅህንም በላዬ አደረግህ።
ትዕቢተኞች ወጥመድን ሰወሩብኝ፥ ለእግሮቼም የወጥመድ ገመድን ዘረጉ፤ በመንገዴም ዕንቅፋትን አኖሩ።
ከጀርባዬ እግዚአብሔር በትሩን እንዲያነሣና ግርማውም እንዳያስፈራኝ እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛ በመካከላችን ምነው በተገኘ!
የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን ሰዎች ይጠብቃል፤ በዙሪያቸውም ሆኖ ከአደጋ ያድናቸዋል።
እግዚአብሔር የእስራኤል መሪዎች የሆኑትን እነዚህን አረጋውያን ሰዎች አልቀሠፈም፤ ይልቁንም እግዚአብሔርን አይተው በፊቱ በሉ፤ ጠጡም።
ዘለዓለማዊ አምላክ መጠጊያህ ዘለዓለማዊ ክንዶቹ ደጋፊዎች ናቸው፤ ጠላትን ከፊትህ ያባርራል፤ እንድትደመስሳቸውም ያደርጋል።
ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤