ትእዛዞችህን ሁሉ በጥንቃቄ ከአስተዋልኩ ኀፍረት ከቶ አይደርስብኝም።
ወደ ትእዛዞችህ ስመለከት፣ በዚያ ጊዜ አላፍርም።
ትእዛዞችህንም ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርምና።
ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገሠች።
በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ በእርሱም ተማምነህ ትኖራለህ።
በሕይወት እኖር ዘንድ በተስፋ ቃልህ መሠረት አበርታኝ! ተስፋዬንም አታጨልምብኝ!
የአንተ ትእዛዞች ትክክል መሆናቸውን ስለማምን የሐሰትን መንገድ ሁሉ እጠላለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! በሕግህ ጸንቼአለሁ፤ እባክህ አታሳፍረኝ።
ኀፍረት እንዳይደርስብኝ ሕግህን በትክክል እንድፈጽም እርዳኝ።
እናንተም እኔ የማዛችሁን ብትፈጽሙ ወዳጆቼ ናችሁ።
ሰው ከትእዛዞች አንዱን አፍርሶ የቀሩትን ሁሉ ቢፈጽም እንኳ ሁሉንም እንዳፈረሰ ይቈጠራል።
እንግዲህ ልጆቼ ሆይ! እርሱ በሚገለጥበት ጊዜ ሳንፈራ በድፍረት እንድናየውና በሚመጣበት ቀን በፊቱ እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፤