Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 119:116 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

116 በሕይወት እኖር ዘንድ በተስፋ ቃልህ መሠረት አበርታኝ! ተስፋዬንም አታጨልምብኝ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

116 እንደ ቃልህ ደግፈኝ፤ እኔም ሕያው እሆናለሁ፤ ተስፋዬም መና ቀርቶ አልፈር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

116 እንደ ቃልህ ደግፈኝ፥ ሕያውም እሆናለሁ፥ ከተስፋዬም አልፈር።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 119:116
16 Referencias Cruzadas  

በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ሞላ ተስፋው አያሳፍርም።


አምላኬ ሆይ! በአንተ እታመናለሁ፤ ጠላቶቼ ድል እንዲቀዳጁ አድርገህ አታሳፍረኝ።


በቅዱስ መጽሐፍ “እነሆ! የተመረጠና ክቡር የሆነ የማእዘን ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ፤ በእርሱም የሚያምን አያፍርም” የሚል ቃል ተጽፎ ይገኛል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።


ነገር ግን አምላክ ረዳቴ ነው፤ ጌታም የሕይወቴ ደጋፊ ነው።


እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም።


የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።


በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፦ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ አያፍርም።”


ወደ አንተ እጠጋለሁ፤ ቀኝ እጅህም ቀና አድርጎ ይደግፈኛል።


እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።


“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።


ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤ በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።


ትእዛዞችህን ሁሉ በጥንቃቄ ከአስተዋልኩ ኀፍረት ከቶ አይደርስብኝም።


በሕይወት እንድኖርና የቃልህን ትምህርት እንድጠብቅ ለእኔ ለአገልጋይህ መልካም ነገር አድርግልኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios