“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።
መዝሙር 111:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚፈሩት ሁሉ ምግባቸውን ያዘጋጅላቸዋል፤ ቃል ኪዳኑንም ከቶ አይረሳም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚፈሩት ምግብን ሰጣቸው፥ ኪዳኑንም ለዘለዓለም ያስባል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኅሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገሩን በፍርድ ይፈጽማል። |
“እግዚአብሔር የሰማይ አምላክ ሆይ! አንተ ታላቅ ነህ፤ እኛም በፍርሃት በፊትህ እንቆማለን፤ አንተ ከሚወዱህና ትእዛዞችህንም ከሚጠብቁ ሁሉ ጋር ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህ።
ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ እንዲህ ስል ጸለይኩ፦ “ለሚወዱህና ትእዛዞችህን ለሚጠብቁ ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ ታላቅና መፈራት የሚገባህ አንተ ጌታ እግዚአብሔር ነህ።