ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።
መዝሙር 109:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል። |
ወደ ኤልሳዕ በቀረበች ጊዜ ግን ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ በመንሣት እግሮቹን ያዘች፤ በዚህ ጊዜ ግያዝ ገፍቶ ሊያስወግዳት ቃጣ፤ ኤልሳዕ ግን “ተዋት፤ ምን ያኽል ጭንቀት እንዳለባት አታይምን? እግዚአብሔርም ስለ እርስዋ ችግር የገለጠልኝ ነገር የለም” አለው።
እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።
ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! ነፍሴ ተጨንቃለች፤ ምን ልበል? ‘አባት ሆይ! ከዚህች ሰዓት አድነኝ ልበልን?’ ይህን እንዳልል ግን እኔ የመጣሁት ለዚህች የመከራ ሰዓት ነው።
እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።