መዝሙር 107:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅኖች ይህን በማየት ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎች ግን ዐፍረው ዝም ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ቅኖች ይህን አይተው ሐሤት ያደርጋሉ፤ ጥመትም ሁሉ አፏን ትዘጋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቅኖች ያያሉ፥ ደስም ይላቸዋል፥ ክፋት በሙሉ አፉን ይዘጋል። |
እግዚአብሔር ድልን ስለሚያጐናጽፈው ንጉሡ ደስ ይለዋል፤ በእግዚአብሔር ስም የሚምሉ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሐሰተኞች አንደበት ግን ይዘጋል።
ነገር ግን በእስራኤላውያንም ሆነ በእንስሶቻቸው ላይ ውሻ እንኳ አይጮኽባቸውም፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በግብጻውያንና በእስራኤላውያን መካከል ልዩነት የማደርግ መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ”
ይህም ሲፈጸም በምታዩበት ጊዜ ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ ሰውነታችሁም እንደ ሣር ይለመልማል፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከአገልጋዮቹ ጋር፥ ቊጣው ግን በሚጠሉት ላይ እንደሚሆን ይታወቃል።”
የሕግ ትእዛዝ የሚመለከተው ከሕግ በታች ያሉትን እንደ ሆነ እናውቃለን፤ በዚህ ምክንያት ሰዎች የሚያመካኙት አጥተው ዝም ይላሉ፤ ዓለሙም ሁሉ በእግዚአብሔር ፍርድ ሥር ይሆናል።