እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፤ አድነን፤ ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እናቀርብ ዘንድ፣ አንተን በመወደስ እንጓደድ ዘንድ፣ ከአሕዛብም መካከል ሰብስበህ አምጣን።
ጌታ አምላካችን ሆይ፥ አድነን፥ ቅዱስ ስምህን እናመሰግን ዘንድ፥ በምስጋናህም እንመካ ዘንድ፥ ከአሕዛብ መካከል ሰብስበን።
እግዚአብሔር ወደ ኢየሩሳሌም መልሶ ባመጣን ጊዜ ሕልም እንጂ እውነት አልመሰለንም ነበር።
ምነው መዳን ለእስራኤል ከጽዮን በመጣ! እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በሚመልስበት ጊዜ፤ የያዕቆብ ልጆች ይደሰታሉ፤ የእስራኤል ሕዝብ ሐሴት ያደርጋሉ።
እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ያድሳል፤ ከእስራኤል የተሰደዱትንም ይመልሳል።
ነገር ግን እኛን ዘወትር በክርስቶስ ድል አድራጊዎች አድርጎ ለሚመራንና መልካም መዓዛ እንዳለው ሽቶ ስለ ክርስቶስ ያለንን ዕውቀት በየስፍራው ሁሉ እንድናዳርስ ለሚያደርገን አምላክ ምስጋና ይሁን!
አምላክህ እግዚአብሔር ምሕረት ያደርግልሃል፤ በአሕዛብ መካከል አንተን ከበታተነበት ስፍራ ሁሉ መልሶ በማምጣት እንደገና ያበለጽግሃል።