በክፉ ሥራቸው እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ በዚህ ምክንያት መቅሠፍት በመካከላቸው ተነሣ።
በሥራቸውም እግዚአብሔርን አስቈጡት፤ መቅሠፍትም በላያቸው መጣ።
በሥራቸውም አስመረሩት፥ ቸነፈርም በላያቸው በዛ።
ዐውሎ ነፋሱንም ጸጥ አደረገ፥ ባሕሩም ዝም አለ።
እነርሱ በሥራቸው ረከሱ፤ በክፉ ሥራቸውም እግዚአብሔርን ካዱ።
እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! ጸሎታቸውን ሰማሃቸው፤ ይቅር ባይ አምላክም ሆንክላቸው፤ ነገር ግን ስለ በደላቸው እነርሱን ከመቅጣት ቸል አላልክም።
መርምሬ የደረስኩበት ሌላው ነገር እግዚአብሔር ሰዎችን ልበ ቅኖች አድርጎ ፈጥሮአቸዋል፤ እነርሱ ግን ተንኰልን ሁሉ ፈለሰፉ።”
በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን በፔዖር ለባዓል ጣዖት በመስገዳቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጣ።
ሰውየውና ሴቲቱ ወዳሉበት ድንኳን ገባ፤ ሁለቱንም በአንድነት በጦር ወግቶ ገደላቸው፤ በዚህም ዐይነት እስራኤላውያንን በማጥፋት ላይ የነበረው መቅሠፍት ቆመ፤
ነገር ግን እስከዚያው ሰዓት ድረስ ያ መቅሠፍት ኻያ አራት ሺህ ሕዝብ አጥፍቶ ነበር።
ከእነርሱ አንዳንዶቹ የዝሙት ኃጢአት እንደ ሠሩ እኛም የዝሙት ኃጢአት እንሥራ፤ እነርሱ ይህን በማድረጋቸው ከእነርሱ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች በአንድ ቀን ሞተዋል።