ዘሮቻቸውን ሁሉ በአሕዛብ መካከል እንደሚጥላቸውና በመላው ዓለም እንደሚበታትናቸው ገለጠላቸው።
ዘራቸውንም በሕዝቦች መካከል ሊጥል፣ ወደ ተለያየ ምድርም እንደሚበትናቸው ማለ።
ደነገጡ፥ እንደ ሰካራምም ተንገዳገዱ፥ ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠ።
እንደሚታረዱ በጎች አደረግኸን፤ በአሕዛብ ምድር በተንከን።
እግዚአብሔር ራሱ የበተናቸው ስለ ሆነ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ እነርሱ አያስብም፤ ለካህናቱ ክብር አይሰጣቸውም፤ ሽማግሌዎችም ልዩ አስተያየት አይደረግላቸውም።
ከዚህም በላይ በተለያዩ አገሮች በሕዝቦች መካከል እንደምበታትናቸው በምድረ በዳ እያሉ በመሐላ አረጋግጬ ነገርኳቸው።
በእናንተም ላይ ጦርነት አምጥቼ በባዕዳን አገሮች ሁሉ እበትናችኋለሁ፤ ሰይፍንም አስመዝዝባችኋለሁ፤ ምድራችሁ ሰው አልባ፥ ከተሞቻችሁም ውድማ ይሆናሉ፤
እግዚአብሔር በሚበትንህ አገሮች የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የደረሰውን ነገር አይተው ይደነግጣሉ፤ መቀለጃና መዘባበቻም ያደርጉሃል።